Home » Sunday sermon – October 13, 2024

በወንጌል የገለጠው የእግዚአብሔር ፅድቅ

Last updated on October 13, 2024 - by Pastor Tariku Eshetu

በአዳም ከሆነብን በክርስቶስ የተደረገልን ይበልጣል ።

ዓላማ

- ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ የድኅነታችን ማዕከል መሆኑን በቃሉ ማፅናት።
- ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ የድኅነታችን ምክንያትና ማዕከል የሆነበትን ምክንያት በቃሉ ማረጋገጥ
- በአዳምና በህግ ከሆነብን ይልቅ በክርስቶስ የተደረገልን እንድሚበልጥ በቃሉ ማረጋገጥ።

መግቢያ

በቀደመው ትምህርት በክርስቶስ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር እንደታረቅን በእርሱም ሰላም እንደ ሆንን እና
አሁንም ስርየትን ባገኘንበት በእርሱ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር እንደምንመካ ተመልክተናል ።
በዛሬው ትምህርት ደግሞ በአዳም ከሆነብን ይልቅ በክርስቶስ የተደረገልን እንደሚበልጥ በቃሉ እንማራለን።

1: የአዳምና የክርስቶስ ንፅፅር።

1:1 አዳም የክርስቶስ አምሳል ነው።
1:2 ለስው ልጆች ጥፋት ምክንያት ነው።
1:3 ክርስቶስ የሰው ልጆች አዳኝ ነው።
1:4 አዳም አመፀ፣በደለና ተላለፈ።
1:5 ክርስቶስ ብዙዎችን ለማፅድቅ ታዘዘ።

2: በአዳም ምክንያት የሆኑብን ነገሮች።

2:1 ኃጥአትና ሞት ወደ አለም ገባ ብዙዎችም ሞቱ።
2:2 ፍርድና ኩነኔ ወደ ሰው ሁሉ መጣ።
2:3 ብዙዎች ኃጢአተኞች ሆኑ።
2:4 ሰወች ህግ የሚከሳቸው ሆኑ።

3: በክርስቶስ የሆነልን እውነት

3:1 የእግዚአብሔር ፀጋና ፅድቅ በክርስቶስ ተሰጠን
3:2 በክርስቶስ በኩል በህይወት ነገስን።
2:3 በክርስቶስ መታዘዝ ፀደቅን።
2:4 ከክርስቶስ የተነሳ ፀጋ ከመጠን ይልቅ በለጠ።

ማጠቃለያ

መፀሀፍ እንደሚያስተምር አዳም የክርስቶስ አምሳል ነውና። በመሆኑም ሰውን ሁሉ ይወክላል። ስለዚህ አሁን አንድ ሰው ኃጢአተኛ ለመሆን ምንም ማድረግ ሳይጠበቅብት የአዳም ልጅ ስለሆነ ብቻ ፅድቅ የጎደለው በኃጢአት ምክንያት የሞትና በፍርድ ኩነኔ ውስጥ ያለ ነው።ስለዚ ከዚህ እንዲድንና የእግዚአብሔርን ፅድቅ በማግኘት እንዲድን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ያስፈልገዋል። ምክንያቱም እርሱ የእግዚአብሔር ፀጋ ና ፅድቅ የሚገኝበት ብቸኛው መንገድ ስለሆነ።በአዳም ከሆነብን በክርስቶስ የተደረገልን ይበልጣልና።

Source: https://cmaeec.com/w...

the cross
Jesus is Lord
John 3:16

Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.