Home » Sunday sermon – September 8, 2024

በወንጌል የተገለጠው የእግዚአብሔር ፅድቅ በህግና በመገረዝ አይገኝም

Last updated on September 8, 2024 - by Pastor Tariku Eshetu

ንባብ ሮሜ 2:17-29

ዓላማ

• ህግና ግርዘትን መቀበል የእግዚአብሔርን ፅድቅ እንደማያስገኝ በቃሉ ማረጋገጥ።
• ህግን ለማይፈፅም ግርዘት እንደማይጠቅመው በቃሉ ማረጋገጥ።

መግቢያ

በቀደመው ትምህርት ለማየት እንደሞከርነው በኃይማኖተኛነት አስተሳሰብ መያዝና በሌሎች ላይ መፍረድ
ከእግዚአብሔር የፅድቅ ፍርድ እንደማያድንና በወንጌል የተገለጠውን የእግዚአብሔር ፅድቅ የማግኘት አስፈላጊነትን አይተን
ነበር።በዛሬው ትምህርት ደግሞ በህግና በመገረዝ የእግዚአብሔር ፅድቅ እንደማይገኝ በቃሉ እንማራለን።

1: በህግና በግርዘት አይሁድ መባልና መገለጫው ሮሜ 2:17-24

1:1 ህግን በመቀበል መደገፍ።
1:2 በእግዚአብሔር መመካት።
1:3 ፈቃዱን ማወቅ ።
1:4 በህግ ትምህርት የተሻለውን ማወቅ።
1:5 በህግ የእውቀትና የእውነት መልክ መያዝ።
1:6 ህግ ለሌላቸው አስተማሪ እንደሆኑ በራስ መታመን።
1:7 በህግ እየተመኩ ህግን በመተላለፍ እግዚአብሔርን ማዋረድ።
1:8 ለእግዚአብሔር ስም መሰደብ ምክንያት መሆን።

2: በህግና በግርዘት መፅድቅ የማይቻልበት ምክንያት ሮሜ 2:25-29

2:1 ህግን ለመፈፅም አለመቻል።
2:2 ህግን ባለመፈፀም ግርዘትን ከንቱ ማድረግ
2:3 በህግና በግርዘት የልብ ግርዘት(መለወጥ) ስለማይገኝ።
2:4 የልብ ግርዘት ብቻ ከእግዚአብሔር ምስጋና ስላለው።

ማጠቃለያ

የእግዚአብሔር ፅድቅ የሚገኝበት መንገድ አንድ ብቻ ነው እርሱም እምነት።ስለዚህ በህግና በግርዘት ከመመካት ይልቅ በወንጌል የተገለጠውን የእግዚአብሔር ፅድቅ እንድንቀበል በእግዚአብሔር ወንጌል እንመን እርሱም ልጁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

Source: https://cmaeec.com/w...

the cross
Jesus is Lord
John 3:16

Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.