Home » Sunday sermon – August 25, 2024

በወንጌል የተገለጠው የእግዚአብሔር ፅድቅ

Last updated on August 25, 2024 - by Pastor Tariku Eshetu

ትምህርት ሶስት:- ኃይማኖተኛነትና የእግዚአብሔር ፍርድ

ዓላማ

- ኃይማኖተኞች በወንጌል ካላመኑ ከፍርድ እንደ ማያመልጡ ማረጋገጥ።
- ኃይማኖተኛነት የሚገለጥባቸውን መታወቂያዎች ማመላከት
- በወንጌል ያላመነ ሁሉ እንደሚፈረድበት በቃሉ ማረጋገጥ።

መግቢያ

በቀደመው ትምህርት እንደተመለከትነው እውነትን በአመፅ የሚከለክሉ ሁሉና ኃይማኖት የለሾች በእግዚአብሔር ፍርድ ስር ወድቀው ስላሉ በወንጌል ማመን እንደሚያስፈልጋቸው ተመልክተን ነበር።በዛሬው ትምህርት ደግሞ ኃይማኖተኞችም
በወንጌል ካላመኑ ከእግዚአብሔር ፍርድ ሊያመልጡ እንደማይችሉ በቅዱስ ቃሉ መሰረት እንማራለን።

1: ከፍርድ የማያድነው ኃይማኖተኛነትና መታወቃያው

1:1 የእግዚአብሔርን ህግ እያወቁ አለማድረግ።
1:2 በኃይማኖተኝነት መታመንና በሌላው ላይ መፍረድ።
1:3 በሌሎች ላይ በፈረዱበት መኮነን
1:4 በኃይማኖተኝነታቸው ከፍርድ እንደሚያመልጡ ማሰብ።

2: ኃይማነተኞች ከፍርድ የማያመልጡባቸው ምክንያቶች ።

2:1 ወደ ንሰሀ የሚመራቸውን የእግዚአብሔርን ምህረት መናቅ።
2:2 የእግዚአብሔርን መቻልና የትዕግስቱን ባለጠግነት መናቅ።
2:3 ንስሀ የማይገባ ጠንካራ ልብ ያላቸው መሆናቸው።
2:4 የእግዚአብሔርን ቁጣ በላያቸው ስለሚያከማቹ
2:5 የሀይማኖት ስራቸው የዘላለም ህይወትን ስለማያስገኝላቸው።

3:የእግዚአብሔር ፍርድና. ህይማኖተኝነት

3:1 ሀይማኖተኞችን(አይሁድን) ተጠያቂ ያደርጋል።
3:2 ሀይማኖት የለሾችን(አህዛብን) ተጠያቃቃ ያደርጋል።
3:3 በሰው ዘንድ. የተሸሸገውን ሁሉ ይገልጣል።

ማጠቃለያ

ሰወች ማለትም ሀይማኖት ያላቸውም ሆኑ የሌላቸው ከእግዚአብሔር ቅን እና እውነተኛ ፍርድ ሊያመልጡ አይችሉም። ምክንያቱም እግዚአብሔር ፃድቅ አምላክ ስለሆነ።ስለለዚህ ሀይማኖተኛውም ሆነ ሀይማኖት የለሹ ከዚህ ፍርድ ለመዳን እንዲችሉ በወንጌል አምነው የእግዚአብሔርን ፅድቅ ማግኘት ያስፈልጋቸዋል።የማዳን ኃይል የተገለጠው በወንጌል ነውና ስለዚህ ሀይማኖተኞች ሳይሆን የወንጌል አማኝ እንሁን። ከእግዚአብሔር ፍርድ እንድናለን!!!

Source: https://cmaeec.com/w...

the cross
Jesus is Lord
John 3:16

Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.