Home » Sunday sermon – September 15, 2024

ያለህግ የተገለጠውን የእግዚአብሔር ፅድቅ ማግኘት

Last updated on September 15, 2024 - by Pastor Tariku Eshetu

ንባብ:- ሮሜ 3:1-31

ዓላማ

- በአይሁድና በአህዛብ ፅድቅን በተመለከተ መበላለጥ እንደሌለ በቃሉ ማረጋገጥ።
- ዓለም ሁሉ ፅድቅን በተመለከተ ከእግዚአብሔር ፍርድ ስር እንዳለ በቃሉ ማረጋገጥ።
- ያለ ህግ የተገለጠው የእግዚአብሔር ፅድቅ የሚገኝበትን መንገድ በቃሉ ማረጋገጥ።

መግቢያ

ባለፈው ትምህርት ለማየት እንደሞከርነው መገረዝም ሆነ ህግን መቀበል ከአህዛብ እንደማይለይ እና እውነተኛ አይሁዳዊነት በመንፈስ የልብ ግርዘት ማግኝት እንድሆነ ተመልክተናል።በዛሬው ትምህርት ደግሞ ያለ ህግ የሚገኘውን የእግዚአብሔር ፅድቅ በተመለከተ ቅዱስ ቃሉ የሚያስተምረውን እውነት እንመለከታለን።

1: የአይሁድ ብልጫ እና የመግረዝ ጥቅም ፅድቅን በተመለከተ ምንድን ነው?

1:1 ፅድቅን በተመለከተ የእግዚአብሔርን ታማኝነት ማረጋገጥ።
1:2 ፅድቅን በተመለከተ የእግዚአብሔርን እውነተኝነት ማረጋገጥ።
1:3 የእግዚአብሔርን ፃድቅነት ማረጋገጥ ።
1:5 ፅድቅን በተመለከተ የእግዚአብሔርን ፈራጅነት ማረጋገጥ ።

2: በፅድቅ ጉዳይ አይሁድና አህዛብ የማይበላለጡበት ምክንያት ምንድ ነው?

2:1 ሁሉም ከኃጢአት በታች ስለሆኑ።
2:2 ዓለሙ ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ስለሆነ።
2:3 የህግን ስራ በመስራት ስጋን የለበሰ ሁሉ ስለማይፅቅ።
2:4 ህግ ኃጢአትን ማስታወስ እንጂ ማፅደቅ አለመቻሉ።

3: ያለ ህግ የተገለጠው የእግዚአብሔር ፅድቅ እንዴት ይገኛል?

3:1 በህግና በነቢያት የመስከረለት ነው።
3:2 ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ ነው።
3:3 ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን የሚገኝ ነው።
3:4 እግዚአብሔር ፃድቅ መሆኑን ያሳየበት ነው።
3:5 በእምነት የሚያፀድቅ አምላክ አንድ ብቻ መሆኑ የተረጋገጠበት ነው።

ማጠቃለያ

ፅድቅ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። ስለዚህ አይሁድም ሆኑ አህዛብ ፅድቅን ለማግኘትና ለመፅደቅ ከፈለጉ መንገዱ በክርስቶስ ኢየሱስ ማመን ብቻ ነው።ከዚህ ውጪ ህግን በመፈፀምም ሆነ በመገረዝ መፅድቅ ስለማይቻል ከፅድቅ አንፃር አይሁድ ምንም ትምክህት ሊኖራቸው አይችልም።ምክንያቱም የተገረዘን ስለ እምነት ያልተገረዘንም በእምነት የሚያፀድቅ እግዚአብሔር የሁሉም አምላክ ነውና።

Source: https://cmaeec.com/w...

the cross
Jesus is Lord
John 3:16

Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.