ለእግዚአብሔር ፍሬ በማፍራት እንኑር
ንባብ:- ሮሜ 7:1-12
ዓላማ
- አማኞች ለእግዚአብሔር ፍሬ ማፍራት እንዴት እንደሚችሉ በቃሉ ማመላከት።
- አማኞች ቅዱስ ፃድቅና በጎ ፍሬን ለማፍራት ምን ማድረግ እንዳለባቸው በቃሉ ማመልከት
- አማኞች በአዲሱ የመንፈስ ኑሮ ለመግዛት እራሳቸውን መስጠት እንደሚገባቸው በቃሉ ማሳሰብ።
መግቢያ
በሮሜ ምዕራፍ ስድስት በወንጌል የተገለጠውን የእግዚአብሔር ፅድቅ በእምነት የተቀበሉ ሁሉ በኃጢአት ላይ የበላይ መሆን የሚችሉበትን የቃሉን እውነት ተመልክተናል ።በዛሬው ትምህርት ደግሞ ለእግዚአብሔር ፍሬ ለማፍራት እንዴት እንደምንችል የቃሉን እውነት እንመለከታለን ።
1: ለእግዚአብሔር ፍሬ ለማፍራት ምን እናድርግ?
1:1 በክርስቶስ ስጋ ለህግ መግደላችንን ማመን።
1:2 ከሙታን የተነሳው እርሱ የእኛ ባለቤት መሆኑን ማመን።
1:3 በአዲሱ የመንፈስ ኑሮ ለመግዛት መፍቀድ።
2: ለእግዚአብሔር ፍሬ እንድናፈራ ህጉን ማውቅ አለብን።
2:1 ህጉ ኃጢአት አለመሆኑን ማወቅ።
2:2 ህጉ ለኃጢአት እንደሚያነቃን ማወቅ።
2:3 ህጉ ቅዱስ ትዕዛዙም ቅድስት፣ፃድቅትና በጎ እንደሆነ ማወቅ።
ማጠቃለያ
በወንጌል የተገለጠውን የእግዚአብሔር ፅድቅ በእምነት የተቀበሉ ሁሉ ለእግዚአብሔር ፍሬ በማፍራት ሊኖሩ ይገባቸዋል። ስለዚህ አማኝ ሁሉ በተናጠል በክርስቶስ ስጋ ለህግ መገደሉን ማመን፣ ከሙታን የተነሳው እርሱ ክርስቶስ የእርሱ ባለቤት መሆኑን ማወቅና ማመን እንዲሁም ለአዲሱ የመንፈስ ኑሮ ለመግዛት መንፈስ ቅዱስን መታዘዝ አለበት። ይህን ሲያደርግ ህጉ የሚጠይቀውን ቅድስና ጽድቅና በጎነት በማፍራት እግዚአብሔርን ማክበር ይችላል። ስለዚህ በዚህ የቃሉ እውነት መሰረት ለእግዚአብሔር ፍሬ በማፍራት እንኑር።
Source: https://cmaeec.com/w...
John 3:16
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.