Home » Sunday sermon – Oct 27, 2024

በወንጌል የተገለጠው የእግዚአብሔር ፅድቅ

Last updated on October 27, 2024 - by Pastor Tariku Eshetu

ኃጢአት አይገዛችሁም

የንባብ ክፍል:- ሮሜ 6:11-14

ዓላማ

- በፀጋ የፀደቁ ሁሉ በኃጢአት የማይገዙበትን ምክንያት በቃሉ ማመልከት
- በፀጋው የፀደቁ ሁሉ ኃጢአት እንዳይገዛቸው ማድረግ እንደ ቃሉ ማድረግ የሚግባቸው ምንድን ነው?
- በፀጋው አምነው የፀደቁ ሁሉ በኃጢአት መገዛትን መምረጥ እንደሌለባቸው ማሳሰብ።

መግቢያ

በቀደመው ትምህርት እንደተመለከትነው በወንጌል የተግለጠውን የእግዚአብሔር ፅድቅ ፀጋውን በእምነት በመቀበል ያገኙ ሁሉ በኃጢአት ፀንተው መኖር እንደማይችሉና በኃጢአት ፀንተው መኖር የማይችሉበትን ምክንያቶች ተመልክተናል ። በዛሬው ትምህርት ደግሞ ፀጋውን በእምነት በመቀበል የእግዚአብሔርን ፅድቅ ያገኙ ሁሉ ኃጢአት እንዳይገዛቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው እና ለምን ኃጢአት እንደማይገዛቸው በቃሉ መሰረት እንመለከታለን።

1: በኃጢአት ላለመገዛት ምን እናድርግ? ሮሜ 6:11-14

1:1 ኃጢአትን በሰውነታችን አናንግስ
1:2 ብልቶቻችንን ለኃጢአት አናቅርብ
1:3 እራሳችንን ለእግዚአብሔር እናቅርብ።

2: ለኃጢአት የማንገዛው ለምንድን ነው? ሮሜ 6:14-15

2:1 ከፀጋ በታች ስለሆንን
2:2 ከህግ በታች ስላልሆንን።

3: ለኃጢአት አለመገዛትን እንዴት እንልለማመድ? ሮሜ 6:15-23

3:1 የፅድቅ ወይም የኃጢአት ባሪያ ለመሆን መምረጥ
3:2 ለተቀበልነው የእውነት ትምህርት መሰጠት።
3:3 ብልቶቻችን እንዲቀሱ ለፅድቅ ባርነት አሁን እራሳችንን ማቅረብ።
3:4 ለእግዚአብሔር በመግዛትና በመቀደስ ፍሬ ማፍራት።

ማጠቃለያ

ፀገውን በእምነት በመቀበል የእግዚአብሔርን ፅድቅ ያገኙ ሁሉ ከኃጢአት ኃይልና እገዛዝ ነፃ ወጥተዋል። ስለዚህ እግዚአብሔርን ለመታዘዝ፣የተቀደሰ ህይወት ለመምረጥ እና የፅድቅ ባሪያ መሆንን መምረጥ ይችላሉ። በህይወታችን ላይ ያለውን የኃጢአት ኃይል የመግደል ኃላፊነት ባይኖረንም ምክንያቱም ባመንን ጊዜ እግዚአብሔር ይህን ስላደረገ።ነገር ግን በህይወታችን ኃጢአትን ስለምናስተናግድበት ሁኔታ ግን ኃላፊነት አለብን። ምክንያቱም በኃጢአት ላይ ድል ማግኘታችን የሚወሰነው በምርጫችን ስለሆነ።

Source: https://cmaeec.com/w...

the cross
Jesus is Lord
John 3:16

Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.