- በክርስቶስ ኢየሱስ የቤዛነት ስራ የተገኘውን አንድነት እንደ ቃሉ መረዳት - በክርስቶስ ኢየሱስ የቤዛነት ስራ ለተገኘው አንድነት የአማኞችን ሀላፊነት ማሳሰብ - በክርስቶስ ኢየሱስ የቤዛነት ስራ የተግኘው አንድነት ከምንና ከማን ጋር ግንኙነት እንዳለው መረዳት።
በክርስቶስ ኢየሱስ የቤዛነት ስራ አምነው የዳኑ ሁሉ እግዚአብሔር ከላከው ሰማያዊ ጥሪ ተካፋይ ሆነዋል። ስለዚህ ከዚህ ጥሪ ተካፋዮች መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ያስፈልጋቸዋል።ይህም ማስረጃ ለጥሪያቸው የሚመጥን ኑሮ መኖር ነው። ይህን እውነት በተመለከተ የቃሉን ትምህርት ቀጥለን እንመለከታለን።
1:1 በክርስቶስ ኢየሱስ የቤዛነት ስራ አንድ አካል መሆን። 1:2 በክርስቶስ ኢየሱስ የቤዛነት ስራ የአንድ ሀገር ዜጋና አንድ ቤተሰብ መሆን 1:3 በክርስቶስ ኢየሱስ የቤዛነት ስራ የእግዚአብሔር መኖሪያ መሆን።
2:1 በትህትና ሁሉ መኖር። 2:2 በየዋህነት ሁሉ መኖር 2:3 እርስ በርስ በፍቅር በመታገስ መኖር።
3:1 የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ። 3:2 ወደ አንድ ተስፋ ስለተጠራን 3:3 አንድ አካል ስለሆን። 3:4 አንድ አምላክ፣መንፈስና ጌታ ስላለን።
በክርስቶስ ኢየሱስ የቤዛነት ስራ አምነው የዳኑት ሁሉ እንድ አካል ሆነዋል። ይህ አንድ አካል ደግሞ ክርስቶስ ራስ የሆነበት ነው። ስለዚህ ይህንን አንድነት በመጠቅ መኖር ይገባናል።የተቀበልነው ጥሪ የአንድነት ጥሪ ነውና። ለተቀበልነው ጥሪ እንደሚገባ እንኑር!!!!
Source: https://cmaeec.com/w...
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.