- የእግዚአብሔር ጥበብ ከሰው ጥበብ እንደሚለይና እንደ ሚበልጥ ማሳሰብ። - የእግዚአብሔርን ጥበብ ማግኘት የሚቻልበትን መንገድ ማመላከት። - አማኞች በእግዚአብሔር ጥበብ ላይ መታመን እንደሚያስፈልጋቸው ማሳሰብ።
ሰወች በዚህ ምድር ሲኖሩ የሚያደርጉት የህይወት ትግል መሰረታዊ አስፈልጎታቸውን ለመገንዝብ የሚያደርጉት ትግል ነው። ለዚህም ከትምህርት ፥ ከተሞክሮና ከፍልስፍና መፍትሄ ለማግኝት ጥረት ያደርጋሉ።ግን እስክ ዛሬ ድርስ አልቻሉም። አማኞች ግን ከዚህ ችግር በላይ ናቸው። እንዴት? የሚለውን ከዚህ ቀጥለን እንመለከታለን።
1:1 በሰው ቃልና ጥበብ ወንጌልን አለመስማት 1:2 ከተሰቀለው ክርስቶስ በቀር ከሌላ እውቀት ነፃ መሆን። 1:3 በመንፈስ ኃይልና መገለጥ ወንጌልን መሰበክ።
2:1 ከዚህች ዓለም ጥበብ ይለያል 2:2 ከዚህች ዓለም ገዥዎች እውቀት ውጪ ነው። 2:3 እግዚአብሔር ለህዝብ ክብር የወሰነውና የሰወረው ነው። 2:4 የሰው ዓይን ያላየው፥ የሰው ጆሮ ያልሰማውና የሰው ልብ ያላሰበው ነው።
3:1 መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ነግር ሁሉ ይመረምራል ያውቃል። 3:2 መንፈስ ቅዱስ አማኞች ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን እንዲያውቁ ያደርጋል 3:3 መንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊዉን ነገር ከመንፈሳዊ ነገር ጋር ማስተያየት ያስችላቸዋል። 3:4 መንፈስ ቅዱስ አመኞችን ያስተምራቸዋል።
የእግዚአብሔር ጥበብ የእርሱ ስጦታ ነው። ይህም በመንፈስ ቅዱስ መገለጥ ብቻ ነው የሚገኘው። በሰው ጥረት ከቶ አይገኝም። ነገር ግን ለአማኞች ደግሞ ነፃ ስጦታ ነው።ስለዚ አማኞች እግዚአብሔርን በመውደድና በመንፈስ ቅዱስ በመመራት ሊመላለሱ ይገባል።በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ጥበብ ለመሞላት እንዲችሉ።
Source: https://cmaeec.com/w...
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.