Home » Sunday sermon – September 29, 2024

በወንጌል በተገለጠው የእግዚአብሔር ፅድቅ አምኖ መፅደቅና ውጤቱ

Last updated on September 29, 2024 - by Pastor Tariku Eshetu

ንባብ ሮሜ 5:1-11

ዓላማ

- በእምነት የእግዚአብሔርን ፅድቅ የመቀበልን ውጤት በቃሉ መገንዘብ።
- በእምነት የእግዚአብሔርን ፅድቅ የተቀበለ ሰው ከዚህ ዓለም መከራና ስደት ጋር ያለውን ግንኝነት በቃሉ መሰረት መረዳት።
- በእምነት የእግዚአብሔርን ፅድቅ የተቀበሉ በእግዚአብሔር እንጂ በስራቸው እንደማይመኩ በቃሉ መሰረት መረዳት።

መግቢያ

በቀደመው ትምህርት እንደተመለከትነው ሰወች የእግዚአብሔርን ፅድቅ በእምነት ብቻ በመቀበልይፀድቃሉ። ይህም የብሉይና የሀዲስ ኪዳን እውነት መሆኑን ተመልክተናል። በዛሬው ትምህርት ደግሞ በእምነት የእግዚአብሔርን ፅድቅ የቀበሉ ሰወች በህይወታቸው የተከሰተውን መንፈሳዊና ዘላለማዊና እውነት በቃሉ መሠረት እንመልከት።

1: በእምነት የእግዚአብሔርን ፅድቅ መቀበል የሚከስተው እውነት።

1:1 ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት በተመለከተ

1:1:1 ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም አድርጎናል።
1:1:2 የእግዚአብሔር የክብር ተስፋ ተካፋይ አድርጎናል።
1:1:3 የእግዚአብሔር ፍቅር በመንፈስ ቅዱስ በልባችን እንዲፈርስ አድርጎአል።

1:2 ከዚህ ዓለም መከራ ጋር ባለን ግንኙነት ደገሞ

1:2:1 በመከራችን ሐሴት የምናደርግ ሰወች አድርጐናል።
1:2:2 መከራችን መንፈሰዊ በስለትን የምናገኝበት እዲሆን አድርጐአል።

2: በእምነት የእግዚአብሔርን ፅድቅ መቀበልና ዘላለማዊ እርግጠኝነት።

2:1 ለዘላለም ፅድቀናል።
2:2 ከእግዚአብሔር የፍርድ ቁጣ ለዘላለም ድንናል።
2:3 በክርስቶስ ህይወት ለዘላለም ድነናልን።
2:4 ከአምላችን ከፈጠሪያችን ጋር ለዛዘም ታርቀናል።
2:5 የእግዚአብሔር ማዳን ለዘላለም አስመክቶና።

ማጠቃለያ

በእምነት የፀደቀ ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም ነው። የእግዚአብሔር የክብር ተስፋ አለው። የእግዚአብሔርም ፍቅር በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በልቡ ፈሶአል።ስለዚህ ከዚህ ዓለም የሚመጣበት መከራ መጥፊያው ወይም የመረገሙ ማስረጃ ሳይሆን በመንፈሳዊ ህይወቱ የሚያድግበትና ደስ የሚሰኝበት ነው።በእምነት የፀደቀ በክርስቶስ ደም በመፅደቁ ከእግዚአብሔር ቁጣ ለዘላለም ድኖአል። ኃጢአቱ ተሰርዮአል ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም ታርቆአል።ይህ ሁሉ በስራው ያገኘው ሳይሆን በእምነት የተቀበለው የእግዚአብሔር ስራ ስለሆነ በእግዚአብሔር ይመካል።

Source: https://cmaeec.com/w...

the cross
Jesus is Lord
John 3:16

Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.